loader image

Special Remarks and Opening Speeches From Her Excellency Mrs. Zehra Humed

Special Remarks and Opening Speeches From Her Excellency Mrs. Zehra Humed

 Her Excellency Mrs. Zahara  Humed,

Deputy Speaker of the House of Federation of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

Center for Development and Capacity Building (CDCB) is profoundly humbled and exceedingly privileged for having you as the guest of honor on the opening of our “ETHIOPIAN YOUTH LEADERS DIALOGUE ON FEDERAL GOVERNANCE, DEMOCRACY, HUMAN RIGHTS AND PEACE” training program.  

The Center for Development and Capacity Building would like to thank you for your inspiring speech. Your speech was motivating and inspiring for our young trainees and your presence is evidence for your commitment to empower youth leadership. While we share your speech, we hope you continue to work with us and keep on inspiring our young leaders.

የተከበሩ ወ/ሮ ባንቺይርጋ መለሰ፡ በፌ/ም/ቤት የመንግስታት ግንኙነት፣ የዲሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ-መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ፀሃፊ፤

የተከበራችሁ የፎረም ኦፍ ፌዴሬሽ አመራሮች፤

የተከበራችሁ የሥልጠናው ተሳታፊዎች

ክቡራንና ክቡራት

በቅድሚያ በዚህ በምክር ቤታችን እና በፎረም ኦፍ ፌዴሬሽንስ አማካኝነት ከፌዴራል አስተዳደር ጋር በተያያዙ ወሳኝ ጉዳዮች ዙሪያ በተዘጋጀው የምክክር አመቻችነት ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁ በራሴና በምክር ቤታችን ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

ኢትዮጵያ አገራችን የረጅም ዘመናት የብዝሃነት፣ የአብሮነትና የመቻቻል ባህልና ታሪክ ያላት አገር ናት፡፡ ይህ ሲባል ግን በታሪክ አጋጣሚዎች ማለትም በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ብዝሃነትንና ሌሎች መልካም እሴቶች ሊሸረሽሩ የሚችሉ አሉታዊ አጋጣሚዎች ተከስተው አያውቁም ማለት ግን አይደለም፡፡ ይልቁንም በበሳል እውቀት አስተሳሰብና እሴቶቻችን ምክንያት ግን ሁሉንም ችግር በማሸነፍ አገራችንን ማስቀጠል ችለናል፡፡ ይህን መሰል ችግሮች በአገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም የዓለም ክፍል ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ግን ህዝቡ የራሱን ባህል፣ ወግና እሴት ይዞ ለማስቀጠል ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ መመከት ይኖርበታል፡፡ ለዚህ ደግሞ እውቀትና ክህሎት አስፈላጊ ናቸው፡፡ እውቀትንና ክህሎትን በሚገባ የሚጠቀም ማህበረሰብ ማንኛውንም ችግር በሰለጠነ መንገድ መሻገር የሚችል ከመሆኑም በላይ የትውልድ ተሻጋሪ ታሪክ ባለቤትም መሆን ያስችለዋል፡፡

እንደሚታወቀው ከአገራችን አጠቃላይ ሕዝብ ብዛት ውስጥ የወጣቶች ድርሻ 29 ከመቶ ይሆናል፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግም፣ አገራዊው የወጣቶች ፖሊሲ ወጣቶች በተደራጀ መልኩ በዴሞክራሲያዊ ግንባታ፣ በመልካም አስተዳደርና ልማት ሥራዎች ውስጥ ሊያደርጉ የሚገባቸውን ተሳትፎ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ነገር ግን፣ ወጣቶች በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በቂ ተሳትፎ አድርገው የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውም እንዲረጋገጥ ከማድረግ አንፃር ውስንነቶች ይስተዋላሉ፡፡ ድህነት፣ የትምህርት ጥራት ጉድለት፣ የዴሞክራሲ ባህል ዕጦት፣ የአካታችነት ክፍተት እና ምቹ ተቋማዊ ሁኔታዎች አለመኖር ለዚህ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በአንፃሩ፣ አዎንታዊ ከሆነው አበርክቷቸው ባሻገር አሉታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በስፋት ሲሰተፉ ይስተዋላል፡፡ በተለያዩየ አገራችን አካባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶችና አለመግባባቶች ዋና ተሳታፊዎች ሲሆኑ ይታያሉ፡፡ የተለየ ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸው አካላትም የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ሲሉ ወጣቶችን ግጭቶችን ለማቀጣጠልና ማባባስ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ምንም እንኳን መልካም ተግባራትን የሚሰሩ ባይጠፉም፣ የማኅበራዊ ሚዲያን ጠቃሚ ላልሆኑ ዓላማዎች የሚጠቀሙ ወጣቶችም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡

የተከበራችሁ የሥልጠናው ተሳታፊዎች

አገራችን አሁን ካለችበት ውጥረትና የደህንነት ስጋት ወጥታ ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ዴሞክራሲ እና ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት ታረጋግጥ ዘንድ ወጣቶች የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ ይህን ሚናቸውን ሊወጡ ከሆነ ደግሞ፣ የአገራቸውን ነባራዊ ሁኔታ ተንትነው መረዳት፣ ችግሮችን ለይቶ ማወቅ እንዲሁም የመፍትሄ ሃሳብ ብለው የሚያስቡትን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ አገራዊ ችግሮች በተናጠል የማይፈቱ እንደመሆናቸውም ከሚመለከታቸው የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት እንዲሁም ከአጠቃላይ ማኅበረሰባቸው ጋር መወያየት፣ መነጋገርና መመካከር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ እውቀትና ክህሎት ይጠይቃል፡፡

ወጣቶች መብታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ፣ ፍላጎታቸው በአገራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲካተት ለማድረግ፣ እንዲሁም በፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊና  ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት ለመሳተፍ እንዲችሉ በነዚህ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን እውቀት ማስፋታቸው የግድ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ግን ከመንግሥትም ይሁን ከማኅበረሰባቸው ጋር የሚያደርጉት ውይይትና ምክክር ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችላቸውን ክህሎት መጨበጥ አስፈላጊ ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

የዚህ ሥልጠና ዋና ዓላማም በአገሪቷ የፌዴራላዊ አስተዳደር፣ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ የሰላም ግንባታ እና የዴሞክራሲ ግንባታ ጉዳዮች ዙሪያ ሠላማዊ ውይይት (dialogue) ለማድረግ የሚያስችል አቅም መፍጠር ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከማሳካት አኳያ በአገራችን የመንግሥት ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያ፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የሙያ ማኅበራት ለተውጣጡ ወጣት ሴትና ወንድ አመራሮችን ከላይ በተጠቀሱት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የአራት ቀናት የአመቻቾች ሥልጠና ፕሮግራም በመቅረጽ ለመተግበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡  

ፕሮግራሙ ከስልጠና በተጨማሪ ሰልጣኞች ወደ ማኅበረሰባቸው ሲመለሱ በጉዳዮቹ ላይ መሰል ውይይቶችን እንዲያደርጉ ኃላፊነትን በመስጠት ለውጤታማ ትግበራውም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡ ሥልጠናውን በአምስት ዙር ለመስጠት የታቀደ ሲሆን በቀጣይ ባሉት ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይታሰባል፡፡ 

የተከበራችሁ የስልጠናው ተሳታፊዎች

ይህ ስልጠና በአገራቸሁ ጉዳይ ለምታደርጉት ንቁ ተሳትፎ ትልቅ ስንቅ ይሆናቸዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ወጣት አመራር እንደመሆናችሁ መጠን፣ በየአደረጃጀታችሁ የሚገኙ አባላትን በማብቃት ትልቅ አቅም ትፈጥራላችሁ ተብሎም ይታሰባል፡፡ ስለሆነም፣ ስልጠናው በከፍተኛ ንቃትና አትኩሮት እንድትካፈሉ አደራ እላለሁ፡፡

በመጨረሻም፣ ይህን ስልጠና ያዘጋጀውን የፎረም ኦፍ ፌዴሬሽን እና ስልጠናውን በመተግበር የተሳተፈውን የልማትና አቅም ግንባታ ማዕከል ላደረጉት አስተዋጽኦ እያመሰገንኩ ስልጠናው በይፋ መከፈቱን አበስራለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

Previous Special Remarks and Opening Speechs From Esteemed Obbo Dassa Bulcha, Forum of Federation Ethiopia Head

Connect With Us

Meskel Square Science and Technology Building 5th Floor

Mon – Fri: 8:00 am – 5:00 pm

P.O. Box: 25024 Code 1000

Join the Community

Get latest CDG news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Copyright © 2022 CDCB | Powered by CDCB