loader image

Special Remarks and Opening Speechs From Esteemed Obbo Dassa Bulcha, Forum of Federation Ethiopia Head

Special Remarks and Opening Speechs From Esteemed Obbo Dassa Bulcha, Forum of Federation Ethiopia Head

 Esteemed Mr. Dassa Bulcha,

Forum of Federation Ethiopia

Center for Development and Capacity Building (CDCB) is profoundly privileged for having you in the designing, planning and your leadership and partnership with your good office in our “ETHIOPIAN YOUTH LEADERS DIALOGUE ON FEDERAL GOVERNANCE, DEMOCRACY, HUMAN RIGHTS AND PEACE” program

On behalf of the Center for Development and Capacity Building, I want to thank you for your motivation and experience proven speech. While we share your speech, we are confident that you continue to work in partnership with us and keep on making a positive influence

 

የወጣት አመራሮች የአሰልጣኞች ሥልጠና መርሀ ግብር (አንደኛ ዙር)

ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ላንድማርክ ሪዞረት፣ ቢሾፍቱ

የመክፈቻ ንግግር

ደሳ ቡልቻ፤ የፎሬም ኦፍ ፌዴረሽንስ ኢትዮጵያ ኃላፊ

የተከበሩ ወ/ሮ ዛሂራ ሁመድ – የኢፌዲሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ

የተከበራችሁ የመንግስት ተቋማት አመራሮች

የተከበሩ አቶ አማኑኤል አድነው – የሲዲሲቢ ኤግዝክዩትቭ ዳይሬክቴር

የተከበራችሁ የሥልጠና መርሀ ግብሩ  ተሳታፊዎች

የተከበራችሁ አሰልጣኞችና አመቻቾች

ክቡራንና ክቡራት!!

ከሁሉም አስቀድሜ በዚህ የወጣት አመራሮች የሥልጠና መርሀ ግብር ላይ ለመሳተፍ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁ በራሴና በፎረሙ ኦፍ ፌደሬሽንስ ስም ላቅ ያለ አክብሮታዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩኝ፣ እንኳን በሠላም መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡ እንኳን ደህና መጣችሁ!!

ክቡራንና ክቡራት!

ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ሥልጠና ፎረም ኦፍ ፌዴሬሽስ ከፌደሬሽን ምክር ቤት እና ከሲዲሲቢ ከተባለ ሀገር በቀል መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በጋራ ማዘጋጀት በመቻላችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል፡፡  

በዚህ አጋጣሚ የፌደረሽን ምክር ቤት (በተለይ ከፍተኛ አመራሮቹ) ሁሌም እንደፎሬም ለሚንሰራቸው ሥራዎች ቀና ትብብርና ከፍተኛ ድጋፍ ስለሚያደረግልን ከፍ ያለ ምስጋናዬንና አክብሮቴን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ!

ሲዲሲቢም ከመነሻው ጀመሮ የሥልጠና መርሀ ግብሩን ለማዘጋጀት አቅደን በአጋሪነት ከእኛ ጋር የሚሰራ ሀገር በቀል ድርጅት በሚናፈላልግበት ወቅት ፍቃደኝነቱን በማሳየት ላለፉት 12 ወራት ከእኛ ጋር በመሥራት መርሀ ግብሩን ዛሬ እውን ስላደረጉልን ሲዲሲቢን እንደድርጅት፤ አመራሮቹና ሠራተኞቹን እንደግለሰብ ከልብ የመነጨ ምስጋና ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡

የዚህን የሥልጠና መርሀ ግብር ወጪን ጨምሮ ላለፉት አምስት ዓመታት ስንሰራ ለቆየናቸው ሥራዎች የፋይናንስ ድጋፍ ላደረገልን የካናዳ መንግስትን ማመስገን ይጠበቅብኛል፡፡

ክቡራንና ክቡራት!

ፎረም ኦፍ ፌደሬሽንስ በፈዴራሊዝም፣ ባልተማከለና አካታች አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰራ ዓለም-አቀፍ ድርጅት ሲሆን፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 የፌደራል ሀገራትን በአባላትነት/በአጋሪነት ያቀፈ የፌዴራል መንግስታት ጥምረት/ድርጅት ነው፡፡

ፎሬሙ ድርጅቱ ከላይ በጠቀስኳቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዓለም አቀፋዊ ልምድና ተሞክሮ ያለው፣ በተለይም የፌደራልዝምና ያልተማከለ የመንግሰት ቅርጽ ያላቸው ሀገሮች እንዲሁም ከግጭት በኃላ በሽግግር ሂደት ላይ በሚገኙ ሀገራት የሀገረ- መንግስት ግንባታ እና የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በማገዝ ይታወቃል፡፡ በሁሉም ክፍለ-ዓለማት ብዝሃነትን የሚያስተናግድ፣  አካታችና አሳታፊ የሆነ የመንግስት ሥርዓት እንድገነባ፤ የፖሊሲ፣ የአቅም ግንባታና ቴክኒካዊ እገዛዎችን የሚያደርግ፤ በተለይም አዳድስ አስተሳሰቦችና እውቀቶችን ከማመንጨትም ባሻገር ንጽጽራዊ የተግባር እወቀቶችና ልምዶችን ያሰራጫል፡፡ ሀገራት እንዲማማሩና ተግባራዊ ልምድና ተሞክሮኣቸውን እንዲለዋወጡ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ በፖሊሲ አውጪዎችና የመስኩ ምሁራን መካከል የእውቀትና የተግባራዊ ተሞክሮ ሽግግር እንዲኖር እንደመድረክ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ፎሬሙ በኢትዮጵያም ላለፋት 13 ዓመታት ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው በፌዴራል አስተዳደር፣ ብዝሃነትና አካታችነት፣ ግጭት አፈታትና ሰላም ግንባታ እና የአመራር አቅም ግንባታ ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሲተገብር ቆይቷል፡፡

ፎሬሙ በዋናነት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ከሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም አግባብነት ካላቸው የፌዴራልና የክልል መንግስታት ተቋማት፣ ከሲቭክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከከፍተኛ የትምህርትና ምርምር ተቋማት ጋር በአጋሪነትና በትብብር የሚሰራ ሲሆን፤ በርካታ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችንና የምክክር መድረኮችን በፌደራልና በክልል ደረጃ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ እንደዚሁም ጥናቶችን በማካሄድ የፖሊሲ ሀሳቦችን ያመነጫል፤ ምክረ-ሀሳቦችን ያቀርባል፡፡

ባለፉት አምስት አመታት የፌዴራል ሥርዓቱን ለማጠናከር እና በሀገሪቱ የተከሰተውን ፖለቲካዊ ለውጥ ለማገዝ የተቋማትና ሥርዓት ግንባታ ላይ አተኩሮ የበኩሉን ለማደረግ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ የተቋማት ግንባታ እና የሠላም ግንባታ ጥረቶችን ለማገዝ በሦሰት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ እነሱም በመንግስታት ግንኙነት ሥርዓት፣ በፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ሥርዓት (በተለይም የፊስካል ግንኙነት ሥርዓት) እና በህገ-መንግስት ትርጉም ሥርዓቱን የሚመለከቱ ሲሆን እስካሁን በተሰሩት ሥራዎች ከፍተኛ ውጤች ተገኝቶባቸዋል፡፡   

ክቡራንና ክቡራት!

ፎረሙ በሚተገብራቸው ፕሮጅክቶችና በሚሰራቸው ሥራዎች ውስጥ የሴቶችንና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ ትኩሬት ያደርጋል፡፡ በዛሬው ቀን የምንጀምረው የወጣት አመራሮች የአሰልጣኞች ሥልጠና መርሀ ግብርም የዚሁ ማሳያ ሲሆን በየደረጃው ለሚገኙ ለሀገራችን ወጣት አመራሮች የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ መርሀ ግብር ነው፡፡

ይህ ለአራት ቀናት የሚሠጠው ሥልጠና ወጣቶች በሀገር ግንባታ እና ሠላም ግንባታ ውስጥ ያላቸውን ቁልፍ ወይም የማይተካ ሚና ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ዋና ዓላማውም ወጣቶች ቁልፍ በሆኑ የሀገራቸው ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ውሰጥ ሰላማዊ፣ ንቁና ውጤታማ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እና በጎ አስተዋጾ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸውን አቅም መፍጠር ነው፡፡ ይህን ማድረግ የሚችሉት ደግሞ በዋናነት በነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ተገቢ እውቀት እና አስፈላጊ የአመራርና የተግባቦት ክህሎቶች ሲኖራቸው ተብሎ ይታመናል፡፡

የሥልጠና ካሪኩሌም ሲቀረጽም መነሻ የተደረገ ነገር ቢኖር በሀገራችን አስተዳደር (ገቨርናንስ) ጉዳዮችና ተግዳሮቶች ዙሪያ የወጣቶቻችን ቁልፍ የእውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን ምንድን ናቸው የሚል ነው፡፡ ይህንን ለመለየትም የዳሰሳ ጥናት እና በርካታ ዉይይቶች በየደረጃው ተገርጓል፡፡ በዚሁ መነሻነት ሥልጠናው በይዜቱ የፌደራልዝምና ህገመንገስት ጉዳዮችን፣ ሰብአዊ መብቶችን፣ የግጭት አመራርና ሠላም ግንባታ ጉዳዮችን፣ እንዲሁም የአመራር፣  የሰላማዊ ተግባቦት እና የምክክር (ዲያሎግ) ክህሎቶችን እንዲያካትት ተደገርጓል፡፡

ሥልጠናው ደረጃቸውን በጠበቁ የሥልጠና ሞጂውሎች የተደገፈ ሲሆን፤ እንዚህም ብቃት ባላቸው የመስኩ ምሁራን የተዘጋጁ፣ በተለያየ ደረጃ የተገምግሙና ተገቢነታቸውና ጥራታቸው የተረጋገጡ ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎች በሚገኝ ግብዓትና አስተያየቶች እየዳበረና እየተሻሻለ የሚሄድ ይሆናል፡፡  የሥልጠናው አሰጣጥም በታወቁ የአዋቂዎች የሥልጠና አሰጣጥ ዘዴዎችን በመጠቀም ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ይሆናል፡፡ 

ክቡራንና ክቡራት!

በዚህ የአሰልጣኞች ሥልጠና መርሀ ግብር 210 ወጣት አመራሮች በአምስት ዙር የሚሰለጥኑ ሲሆን፤ እነሱም ወደየተቋሞቻቸው ሲመለሱ በጠቅላላው ከ10ሺ ያላነሱ ወጣቶችን ያሰለጥናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተሳታፊዎች አግባብነት ካላቸው የፌደራልና ክልል መንግስታዊ ተቋማት፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ሀገር በቀል ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሚዲያ ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች፣ ወዘተ  የተዉጣጡ፤ ግልጽ መስፈርቶች ተቀምጦ እና ረጅም ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ የተለዩና የተመረጡ ወጣት አመራሮች ናቸው፡፡

ተሳታፊዎቹ በዚህ ሥርዓት ተመርጠው እንዲመጡ ስደረግ ታሳቢ የተደረገው ሥልጠናውን ከራሳቸው ጥቅምና አቅም ማጎልበቻ ባሻገር  ለሌሎች ወጣቶች ጭምር መሆኑን አውቀው ይሳተፋሉ የሚል ነው፡፡ በመሆኑም ተሳታፊዎች ሥልጠናውን በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜትና በንቃት በመከታተል የግል አቅማቸውን ከማሳደግ ባሻገር እዚህ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ለሌሎች ወጣቶች በማስተላለፍ የሥልጠና መርሀ ግብሩን ዓላማ ያሳካሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ስለሥልጠናው ይህንን ካልኩኝ፤ ክቡራን ተሳታፊዎች! ሥልጠናው የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የእናንተ ንቁ ተሳትፎና አስተዋጽኦ ወሳኝ ስለሆነ፤ ሥልጠናውን በከፍተኛ ሥነ ምግባር እንደሚትከታተሉ እና የነቃ ተሳትፎ እንደሚታደርጉ ያለኝን ሙሉ እምነት እየገለጽኩኝ፤  

ክብርት ወ/ሮ ዛሂራ ሁመድ የፌ/ም/ቤት ምክትል አፌ-ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉልንና የሥልጠና መርሀ ግብሩን በይፋ እንዲከፍቱልን በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

መልካም የሥልጠና ጊዜ!!

Previous Dialogue Forum on Youth Leadership under way​

Connect With Us

Meskel Square Science and Technology Building 5th Floor

Mon – Fri: 8:00 am – 5:00 pm

P.O. Box: 25024 Code 1000

Join the Community

Get latest CDG news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Copyright © 2022 CDCB | Powered by CDCB