ድርጅታችን ሴንተር ፎርዴቬሎፕሜንት ኤንድ ካፓሲቲ ቢልዲንግ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ቅድሚያ ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲዲሲቢ በሰብአዊ መብት ጉዳዮች, በሰላም መስፈንና በመልካም አሰተዳደር ረገድ በማህበራዊ ሚዲያ በሚገባ ለመገልገል እንዲያስችለው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ‘የመስመር ላይ ወጣት ማህበረሰብን’ አቋቋሟል፡፡ በዚህ ረገድ የሰብአዊ መብት አያያዝን ለማጠናከርና ብዙ ተከታይ ወጣቶችን አፍርቶ የበለጠ ተዕእኖ ለመፍጠር እንዲቻል ሚያዝያ 2015 ዓ.ም. የማህበራዊ ሚዲያ (ፌስቡክ) ወር ብለን ሰይመናል፡፡ እንቅስቃሴው ወድድርን/ፈተናን (challeges) , ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥንና የምክክር ዐውደጥናቶች ያካትታል፡፡ ይህ ዐውደጥናት የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን አያያዝን በማሳደግና በመከላከል ረገድ በባለድርሻ አካላት አመራር እና በወጣቱ ዘንድ የብዙሃን የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኝ የማህበረሰቡን የተባበረ ጥረት የመሳብ አካል ነው፡፡



ማዕከሉ ለሰብአዊ መብት ጉዳዳች ቅድሚያ የሰጠው ለሰላም ግንባታና በአገርአቀፍ ደረጃ በተለያዩ ማህበረሰቦች ዘንድ መተማመንን ለመፍጠር በማሰብ ነው፡፡ የሰብአዊ መብት ጥሰት ያለ ጥርጥር ወደ አለመግባባትና ሽብር የሚያመራ በመሆኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች የሲዲሲቢ ብቻ ሳይሆን በይበልጥም በመንግስትና በሌሎች ባለድርሻ አካላትም ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡ ሽብር በሰዎች ሞትና በንብረት ውድመት የሚከሰት ጥፋትን ያስከትላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጥፋት ደግሞ በተደጋጋሚ ሽብርን በሽብር የመመለስ መበቃቀልና የማህበረሶችን መበታተን ሊያስከትል ይችላል፡፡
በመሆኑም ሲዲሲቢ ከለጋሽ ድርጅቶች በተለይ ከናሽናል ኢንዶውሜንት ፎር ዲሞክራሲ (ኔድ) እና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር በዲጅታል መድረክ አማካይነት የሕዝቡን የንቃት ደረጃ ለማሳደግ በሰፊው ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የዚህ ዐውደጥናት ውጤትም የሰብአዊ መብትን አያያዝ በማጠናከር ዘላቂ የሆነ በጎ ተዕእኖ ለመፍጠር በሁሉም የሚዲያ አውታሮች በተደጋጋሚ እንደሚሰራጭ ተስፋ እናደርጋለን፡፡