loader image

በማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች መካከል የተደረገ ምርክክር

በማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች መካከል የተደረገ ምርክክር

ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት ኤንድ ገቨርናንስ (ሲዲጂ) በሰብአዊ መብቶች ፥ በሕግ የበላይነት እና መልካም አሰተዳደር ጉዳዮች ላይ ከ80 በላይ በሚሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ  ተጽእኖ ፈጣሪዎች መካከል ለሶስት ዙሮች ምክክር አካህዷል። የምክክሩ ተሳታፊዎች የተውጣጡት  አግባብነት ካላቸው የተለያዩ የመንግሰት ተቋማት፥ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፥ ከሚዲያ  ተቋማትና  የማበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ግለሰቦች ነበሩ፡፡  በአዲስ አበባ ከተማ በጥር ወር  የተካሄደው ምክክር በሶስቱ ጽንሰ ሀሳቦች ላይ የህግ ባለሙያ  በሰጠው ማብራሪዎች መነሻ ነበር፡፡ ባለሙያው በማብራሪያዎቹ ሶስቱ ጉዳዮች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መሰረት መሆናቸውን በአንክሮ አስገንዝቧል፡፡ ከገለጻው በኋላ በነበረው የውይይት ጊዜ ተሳታፊዎቹ በርእሰ ጉዳዮቹ ላይ በንቃት ተሳተፏል፡፡ የውይይቱ ውጤቶችም የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የጠቆሙና ሰብአዊ መብቶችን በማስፈን ፥ የሕግ የበላይነትን በማስከበር እና መልካም አሰተዳደር በማስፈን ረገድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የሚኖራቸውን ሚና ያመላከተና ተሳታፊዎቹም በግላቸዉ የበኩላቸዉን ድርሻ ለመወጣት ቃል የገቡበት ነበር፡፡

ሲዲጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰላም ጉዳዮች ላይ የሕዝቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በሚረዱ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ልዩ ትኩረት የሰጠውም  የማህበራዊ ሚዲያ ሥርጭት ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች በሰላም ጉዳይ ላይ በጎ ተጽእኖ መፍጠር በማስቻሉ ላይ ነው፡፡ ድርጅቱ የምክክሩን ዉጤቶችን በጽሑፍ ፥ በአጫጭር ፊልሞች እና በዲዛይን አቀናጅቶ ለሥርጭት አዘጋጅቷል፡፡ እነዚህ ዉጤቶችን በሚቀጥለው አንድ ወር ወይም ሁለት ወራት በተለያዩ ማህበረዊ ሚዲያዎች አማካይነት የሚሰራጩ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በሚቀጥሉት ቀናት የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቹ እነዚህን ድንቅ ሥርጭቶች እንዲከታተሉ ሲዲጂ ከወዲሁ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Previous CDG Conducted Dialogue among Social Media Influencers

Connect With Us

Meskel Square Science and Technology Building 5th Floor

Mon – Fri: 8:00 am – 5:00 pm

P.O. Box: 25024 Code 1000

Join the Community

Get latest CDG news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Copyright © 2022 CDCB | Powered by CDCB